October 2 2024
Diaspora news
ፍራንክሬሚት" : አዲስ የገንዘብ መላኪያ አገልግሎት ይፋ ሆነ
የሳንቲምፔይ መስራችና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ትንሳኤ ደሳለኝ በመርሐግብሩ ላይ እንደገለጹት፣" የፍራንክሬሚት ዋና ዓላማ 'በአይን ጥቅሻ በሴኮንድ ሽርፍራፊ በሚባል ቅጽበት' ገንዘብ መላክ የሚያስችል ፈጣን አገልግሎት መስጠት ነው። ይህ አዲስ መድረክ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ገንዘባቸውን በቀላሉ እና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲልኩ ያበረታታል" ብለዋል። ፍራንክሬሚት በኢትዮጵያ በአይነቱ ልዩ የሆነ የገንዘብ መላኪያ መንገድ ሲሆን፣ ከባህር ማዶ ገንዘብ መላክን ቀላል፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ግልፅ ያደርገዋል።
ፍራንክሬሚት በውጭ ሀገራት ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት ገንዘብ የመላክ ሂደትን ለማቀላጠፍ ያለመ ሲሆን፣ ገንዘብን በፍጥነት እና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ወደ ሁሉም የኢትዮጵያ ባንኮች፣ ቴሌብር፣ ሲቢኢብር እና ኤም-ፔሳ መላክ ያስችላል።


ተጠቃሚዎች ገንዘብ ለመቀበል ቀናትን መጠበቅ ሳያስፈልጋቸው፣ ገንዘብ ሲላክላቸው በሴኮንድ ውስጥ በማንኛውም የባንክ አካውንት መቀበል ይችላሉ። ይህ የማስጀመሪያ ፕሮግራም ፍራንክሬሚት ለሌሎች በተመሳሳይ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ተቋማት የመተዋወቂያ እና አብሮ ስራ የመጀመሪያ ክንውን ይሆናል ተብሏል።
Write a Comment
Search Here
comment